=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ጉዳዮችን ለአሏህ በመተው ፤ በሱ መማካት ፤ ቃሉን ማመን ፤ ፍርዱን መቀበል ፤ በሱ መተማመን እና የችግሮቻችንን መፍትሔ ከሱ መጠበቅ እጅግ ከላቁ የኢማን ፍሬዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ታላላቅ ከሆኑ የሙእሚኖች ባህሪም ውስጥ ይቆጠራል። አንድ የአሏህ ባሪያም የጉዳዮቹ ፍፃሜ ያማረ መሆኑን አውቆ ሲረጋጋና በሁሉም ጉዳዮቹ በጌታው ሲመካ እንክብካቤን ፣ ቀረቤታን ፣ ድጋፍንና ድልን ያገኛል። ኢብራሂም(ዐ.ሰ) እሳት ውስጥ ሲወረወሩ «ሐስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል» አሉ። በዚህም አሏህ እሳቷን ቀዝቃዛና ሰላም አደረገላቸው። መልእክተኛችንም(ሰ.ዐ.ወ) እና ባልደረቦቻቸው በከሃዲዎችና በጣኦት አምላኪ ጦረኞች ሲከበቡ «ሐስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል» አሉ።
--<({አል-ቁርአን 3:174})>--
«ከአሏህም በሆነ ፀጋና ችሮታ ክፉ ነገር ያልነካቸው ሆነው ተመለሱ ፤ የአሏህን ውዴታ ተከተሉ አሏህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።»
የሰው ልጅ ብቻውን ክስተቶችን ታግሎ ማሸነፍና ችግሮችን መቇቇም አይችልም። ምክኒያቱም ደካማና መላ-ቢስ ተደርጎ ተፈጥሯልና። ሆም በጌታው ሲመካና ጉዳዮቹን በሙሉ ወደሱ ሲያስጠጋ ከሚሸሸው ነገር ሊድን ይችላል። አለበለዚያ መከራዎች ሲፈራረቁበት እና ችግሮች ሲያካብቡት የዚህ ድሃና ደካማ ባሪያ መላው ምን ሊሆን ይችላል?
--<({አል-ቁርአን 5:23})>--
«ምእመናንም እንደኾናቸው በአሏህ ላይ ተመኩ አሉ»
በመሆኑም ነፍህን መገሰፅ የምትፈልግ ሆይ! ኃያል ብርቱና የፀጋ ባለቤት በሆነው አሏህ ተመካ፤ ከጭንቀት እንዲያላቅህና ከችግሮች እንዲያድንህ የዘወትር መፈክርህና ድስኩርህ «ሐስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል» ይሁን። ገንዘብህ ቢቀንስ ፣ ብድር ቢጠራቀምብህ ፣ የገቢ ምንጮችህ ቢደርቁ «ሐስቡነሏህ ወኒእመል ወኪል» ብለህ ተጣራ፤ በሽታ ቢይዝህ ስቃይ ቢበረታብህ ችግሮች ቢደራረቡብህ «ሐስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል» በል። የጠላትህን ሴራ ከፈራህ ወይም በደለኛን ከሰጋህ ወይም ድንገተኛ ክስተት ካስደነገጠህ «ሐስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል» በል።
--<({አል-ቁርአን 25:31})>--
«መሪም ረዳትም በጌታህ በቃ»
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|